እማማ ሙላቷ ላንቴ

የ 84 እድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ዛሬ ላይ በሚኖሩባት አንዲት ደሳሳ ጎጆዋቸው ላይ ለብቻቸው ይተክዙ እንጂ የ7 ልጆች እናት ነበሩ ታዲያ ይደግፉኛል ይጦሩኛል ብለው ያሳደጓቸው 7 ልጆቻቸው በውትድርና፣በህመም እና በአደጋ አጥተዋል ዛሬ እኚህ እናት ከሀዘን ብዛት ሁለቱም አይኖቻቸው ማየት አይችሉም የአይን ብርሀን ከማጣታቸው በተጨማሪ ምንም አይነት ረዳት እና ደጋፊ ባለመኖሩ ማህበራችን እኚህን እናት ጎዳና ወጥተው ከመለመን ታድጓቸዋል በማህበራችንም የምግብ ፣የአልባሳት ፣የመጠለያ ፣የህክምና እና እነዚህን የመሳሰሉ ድጋፎች እየተደረገላቸው ይገኛል ፡፡